Bega 2021-22_outlook (Seasonal)


ባለፈው የክረምት ወቅት ለክረምት ዝናብ መጠናከርና መስፋፋት አስተዋጽኦ የሚያደረጉ አካባቢያዊና ዓለም አቀፋዊ ገጽታዎች በከባቢ አየር ውስጥ ምቹ ሁኔታን በመፍጠራቸው የክረምት ዝናብ በወቅቱ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከመደበኛዉ ጋር የተቀራራበ ዝናብ እንዲኖር ምክንያት ሆኗል። ያለፈው ክረምት ዝናብ በአገባብ ረገድ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ መደበኛውን ፈር የተከተለ ሲሆን፤ በአወጣጥ ረገድ ግን ከመካከለኛውና ከምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ለተወሰኑ ቀናት መዘግየት አሳይቷል።

መጪው የበጋ ወቅት አማራ፣ ትግራይ፣ አፋር እንዲሁም የሰሜን ሶማሌና የቤኒሻኒጉል-ጉሙዝ ክልል፣ መካከለኛዉና ምስራቅ ኦሮሚያ አካባቢዎች ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ የማግኘት ዕድል ከፍተኛ ሲሆን፤ በአንጻሩ የደቡብ አጋማሽ የቤኒሻኒጉል-ጉሙዝ፣ ምእራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አካባቢዎችን ጨምሮ መደበኛና ከመደበኛው በታች ዝናብ እንደሚኖራቸዉ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የሶማሌ ደቡባዊ አጋማሽና የደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች በአብዛኛው ከመደበኛው በታች ዝናብ እንደሚኖራቸዉ ይጠበቃል።